ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በንግስት ኤልሳቤጥ 2ኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን በለንደን በመገኘት ገለጹ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ

መስከረም 9/2015 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤጥ 2ኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን በለንደን በመገኘት ገለጹ።

ፕሬዝዳንቷ በንግስቷ ህልፈት በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ሀዘናቸውን ለመግለፅ ለንደን ሂትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቤኪንግሃም ቤተመንግስት ተወካዮች እና የኢትዮጵያ ኤምባሲ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ለንግሥቲቱ በተዘጋጀ የሀዘን መግለጫ መዝገብ ላይም ሀዘናቸውን ገልፀዋል።

ንጉስ ቻርለስ ሦስተኛ በቤኪንግሃም ቤተመንግስት ባዘጋጁት የእራት ግብዣ ላይም መገኘታቸውን በለንደን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ንግስት ኤልሳቤጥ 2ኛ ዛሬ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው የሚፈጸም ሲሆን ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ርዕሰ ብሄሮች፣ መሪዎች እና የንጉሣውያን ቤተሰቦች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW