አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ ሜዳልያ አስገኘች

ነሀሴ 01/2013 (ዋልታ) – በቶኪዮ ኦሊምፒክ 10 ሺህ ሜትር ቨየሴቶች የሩጫ ውድድር አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳልያ አስገኝታለች።

አትሌት ለተሰንበት ውድድሩን 3ኛ በመሆን አጠናቃለች።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን ሁለተኛ ወርቋን በቶኪዮ ኦሎምፒክ ስታገኝ ባህሬናዊቷ ቃልኪዳን ገዛኸኝ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች ።

ሌላኛዋ አትሌታችን ፀሀይ ገመቹ ዘጠነኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች ።

ትዉልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን በቶኪዮ በ5ሺ ወርቅ  በ1ሺህ 5መቶ ነሀስ ማግኘቷ ይታወሳል