በሶማሊያ 36 መንገደኞችና የበረራ ሰራተኞች ከአውሮፕላን አደጋ ተረፉ

ሐምሌ 12/2014 (ዋልታ) በሶማሊያ 36 መንገደኞችንና የአውሮፕላን የበረራ ሰራተኞች አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው አውሮፕላን በሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ ተከሰከሰ፡፡

አውሮፕላኑ ሞቃዲሾ አየር ማረፊያ እያረፈ በነበረበት ወቅት አደጋ ደርሶበት በግዳጅ ያረፈ ሲሆን በመንገደኞች ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስ ማትረፍ መቻሉን የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታውቀዋል፡፡

አውሮፕላኑ ሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ ለማረፍ ባደረገው ሙከራ ከመንደርደሪያ ወጥቶ ቃጠሎ እንደደረሰበት በማኅበራዊ ሚዲያ እየወጡ ያሉ ምስሎች ያሳያሉ፡፡

የጁባ ኤርዌይስ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ከባይዶዋ ወደ ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በረራ እያደረገ እንደነበርም የአገሪቱ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ያወጣው መግለጫ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW