አቶ ደመቀ መኮንን ከጆ ባይደን የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ጋር በስልክ ተወያዩ

አቶ ደመቀ መኮንን
መጋቢት 30/2013 (ዋልታ) – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ጋር በስልክ ተወያዩ፡፡
አቶ ደመቀ በትግራይ እየተሸሻለ ስላለው ሁኔታ ለብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ማብራራታቸውን አስታውቀዋል፡፡
እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ሰሞኑን በተካሄደው በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያም ውይይት አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንደሚያገኝ እንዳረጋገጡላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/waltainfo
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!