አንጋፋው ድምፃዊ እና የማንዶሊን ተጫዋች አርቲስት አየለ ማሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አርቲስት አየለ ማሞ

መጋቢት 29 /2013 (ዋልታ) – አንጋፋው ድምፃዊ፣ የዜማ እና የግጥም ደራሲ እንዲሁም ማንዶሊን የተሰኘው የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች አርቲስት አየለ ማሞ ባጋጠመው ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

አርቲስት አየለ ማሞ ለበርካታ አንጋፋ እና ወጣት ድምፃውያን ግጥም እና ዜማ በመስጠትም ይታወቃል።
አርቲስቱ እራሱ ማንዶሊን እየተጫወተ ባዜመው “ወይ ካሊብሶ” በተሰኘ ሥራው ይታወቃል።
አርቲስት አየለ ማሞ ግጥም እና ዜማ ሥራ ከሰጣቸው አንጋፋ እና ወጣት ድምፃውያን መካከል ጥላሁን ገሠሠ፣ መሐሙድ አህመድ፣ ብዙነሽ በቀለ፣ ኩኩ ሰብስቤ፣ ኤፍሬም ታምሩ፣ ሀመልማል አባተ፣ ብፅአት ስዩም፣ ወረታው ውበት፣ አስቴር ከበደ፣ እያዩ ማንያዘዋል፣ ሻምበል በላይነህ፣ ደረጀ ደገፋው፣ ጌታቸው ጋዲሳ እና ህብስት ጥሩነህ ይጠቀሳሉ።
የአየለ ማሞ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ተገልጿል።