አዋሽ ባንክ በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዋሽ ባንክ

የካቲት 25/2015 (ዋልታ) አዋሽ ባንክ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።

አዋሽ ባንክ ባለፈው ዓመትም በቦረና እና ጉጂ ዞኖች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 60 ሚሊየን ብር መለገሱን ከባንኩ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ባንኩ ከዚህ ቀደም በምዕራብ ኦሮሚያ ተከስቶ በነበረው ግጭት ተፈናቅለው ለነበሩ ዜጎችና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ቤት ለፈረሰባቸው ዜጎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንም አስታውሷል።