መስከረም 26/2014 (ዋልታ) በወርሃ መስከረም በድምቀት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ዳራ ያላቸው የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓል ተጠቃሽ ናቸው።
የመስቀልና የኢሬቻ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የአዲስ ምዕራፍ የመንግስት ምስረታ በዓል በደማቅ ሁኔታ መካሄዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
በዓት ሰላምና ፀጥታ በሰፈነበት ሁኔታ እንዲከበር የበኩሉን ድርሻ ለተወጣው የአዲስ አበባ ነዋሪ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል።
ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር የሰላምና ፀጥታውን ሁኔታ እንዳስጠበቀም ተገልጿል።
በተሰጠን ኃላፊነት ህብረተሰቡን በሚመጥን መልኩ እንሰራለን ያሉት ከንቲባዋ፣ አዲስ አበባ ላካሄደቻቸው ታላላቅ ሁነቶች ህብረተሰቡ ላሳየው ጨዋነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በሃኒ አበበ