አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በሐረሪ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት ጥገና አስጀመሩ

ሐምሌ 27/2013 (ዋልታ) – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በሐረሪ ክልል ተገኝተው የአቅመ ደካሞችን ቤት ጥገና አስጀመሩ።

በተጨማሪም አፈ ጉባኤው ዛሬ በክልሉ ተገኝተው ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በስነ ስርአቱ ላይ የክልሉ ርእሰ መስተደድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል አመራሮች ተገኝተዋል።