ኡራጋይ ከደቡብ ኮሪያ ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቀቀ

ኡራጋይ ከደቡብ ኮሪያ

ኅዳር 15/2015 (ዋልታ) በኳታሩ የዓለም ዋንጫ የምድብ መክፈቻ ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ሲደረጉ ኡራጋይ ከደቡብ ኮሪያ ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል።

ቀን 10 ሰዓት በኢዱኬሽን ሲቲ ስታዲየም በተደረገው የምድብ 8 ጨዋታ ኡራጋይ ከደቡብ ኮረያ 0 ለ 0 ተለያይተዋል።

በጨዋታው የማሸነፍ ቅድመ ግምትን አግኝታ የነበረችው ኡራጋይ በደቡብ ኮሪያ ተጫዋቾች የተጠናከረ አጨዋወት ነጥብ ለመጋራት ተገዳለች።

በጨዋታው ዳርዊን ኑኔዝ በርካታ የግብ ሙከራዎችን ቢያደርግም በደካማ አጨራረስ ኳስን ከመረብ ማገናኘት አልቻለም።

ደቡብ ኮሪያም በሰን ኦንግ ሚን እና በሌሎች ተጫዋቾች የግብ ሙከራ አድርገው ነበር።

በቀጣይ ጋና ከደቡብ ኮሪያ ኡራጋይ ከፖርቹጋል ሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

በትዝታ ወንድሙ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW