ኢትዮጵያና እስራኤል የኮቪድ- 19 ክትባትን በጋራ ሊያመርቱ መሆኑ ተገለጸ

ሰኔ 24/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ እና እስራኤል የኮቪድ- 19 ክትባትን በጋራ በኢትዮጵያ ሊያመርቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ፣ ምክትል አምባሳደር ኦር ዳንኤሊ እና የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤናው ዘርፍ አብሮ ለመስራት ላይ በማተኮር  ውይይት ማድረጋቸውን በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ መረጃ አመላክተቷል፡፡

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በኢትዮጵያ የኮቪድ- 19 ክትባት በጋራ ለማምረት በሚቻልበት ሁኔታ፣ የአቅም ግንባታ፣ የጤና ዘርፍ ኢንቨስትመንት እና በሁለቱ ሀገራት ጤና ሚኒስቴር መካከል ትብብር ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት አድርገዋል።