ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰባት የአፍሪካ አገሮች 27 ሕፃናት በእስራኤል የልብ ቀዶ ህክምና ሊደረግላቸው ነው

ሰኔ 15/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰባት የአፍሪካ አገሮች 27 ሕፃናት የሕይወት አድን የልብ ቀዶ ህክምና ለማድረግ እስራኤል መግባታቸው ተገለጸ።

በእስራኤሉ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት “ሴቭ ኤ ቻይልድስ ኸርት” የሕይወት አድን የልብ ቀዶ ህክምና ለማካሄድ አፍሪካውያን ህጻናት እስራኤል መግባታቸውን በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ አስታውቋል።

“ሴቭ ኤ ቻይልድስ ኸርት” በመላው አለም በልብ ህመም የሚሰቃዩ ህጻናትን ህክምና በመስጠት የሚረዳ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ነው።