ኢትዮጵያ በትንሳዔ ጉዞ ላይ ናት – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

ሐምሌ 12/2013 (ዋልታ) – የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር ውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ ኢትዮጵያ በትንሳዔ ጉዞ ላይ ናት ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

“እዉነትን ይዘን በራሳችን አቅም ድህነትን ድል ለመንሳት የጀመርነው መንገድ ፍፃሜው ላይ እየደረሰ ይገኛል” ብለዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ መላው የከተማችን ነዋሪዎች እንዲሁም በመላው አለም የምትገኙ የአገሬ ልጆች እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡