ነሐሴ 17/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ በ2014 በጀት ዓመት በጅቡቲ ወደብ በኩል 7.9 ሚሊየን ቶን ደረቅ ጭነት ማስተናገዷ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የ2014 ዓመታዊ ክንውን እና 2015 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በመግለጫው እንዳስታወቀው በ2014 በጀት ዓመት በጅቡቲ ወደብ በኩል 7.9 ሚሊየን ቶን ደረቅ ጭነት አገልግሎት ሰጥቷል።
ድርጅቱ ይህንን ጭነት አገልግሎት ማስተናገድ የቻለው ገቢና ወጪ ጭነት በባሕር በማጓጓዝ፣ በውጭ አገራት ወደቦች መካከል ጭነት በማመላለስ፣ በመልቲሞዳል ወደ አገር ውስጥ ኮንቴነርና ተሽከርካሪ በማጓጓዝ፣ በዩኒሞዳል ገቢና ወጪ ዕቃ በማስተላለፍ፣ በአገር ውስጥ ወደቦች ኮንቴነርና ተሽከርካሪዎች በማስተናገድ እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡
በዓመቱ የተስተዋለው የዓለም የንግድ ሚዛን መዛባት ችግር ቢኖርም ድርጅቱ የወጪ ገቢ ንግድ ማቀላጠፍ ረገድ በ2014 በጀት ዓመት ጥሩ አፈፃፀም ማሳየት መቻሉ በመግለጫው ተነስቷል።
በደረሰ አማረ
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW