ኢትዮጵያ በ2021 በቴክኖሎጂ ቀዳሚ ከሆኑ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች

ሰኔ 10/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ ከቆሻሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ላይ በሰራችው ስራ በ2021 በቴክኖሎጂ ቀዳሚ ከሆኑ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች።

ኢትዮጵያ በኢኖቬሽን ዘርፍ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እየሰራች መሆኑን ተከትሎ ቆሻሻን ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል በመቀየርና ፈጠራ በታከለበት የከተማ ፓርክ ልማት ስራዋ በዚህ ዝርዝር ውስጥ እንድትካተት አድርጓታል ተብሏል፡፡

የአለም ኢኮኖሚ ፎረም ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ፣ ዚምባብዌ፣ የተባበሩት አረብ ኢሜሬትስና ኤልሳልቫዶር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በዚህ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት።

በዚህ አመት በወጣው መረጃ መሰረት ከተመረጡት ኩባንያዎች ውስጥ 30 ከመቶዎቹ እየተመሩ ያሉት ደግሞ በሴቶች ነው ተብሏል።

ዚምባብዌ በማንነት አስተዳደር ቴክኖሎጂ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የመካከላኛው ምስራቅ የባሉበት የፋይናንስ ትምህርት፣ ኤልሳቫዶር ደግሞ የባለ ብዙ የሁልጊዜ የምርትና አገልግሎት ገበያ ቦታ ላይ በሰሩት ስራ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ100 ዝርዝር ውስጥ ተካትተዋል።

ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው በዚህ አመት ከወጣው ዝርዝር ውስጥ አሜሪካ በበርካታ አዳዲስ ስራዎች ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች።

የመረጃ መረብ ደህንነት፣ የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ፣ በጤናና የገንዘብ ተቋማት ላይ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የተዘረጉ የሰው ሰራሽ አስትውሎ ስራዎች፣ የቴክኖሎጂ የፋይናንስ ተቋማት፣ የአረንጓዴ ልማት ቀዳሚ መመዘኛዎች ተደርገዋል፡፡