በሚዛን አማን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ችግኝ ተከላ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 10/2013 (ዋልታ) – በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት “ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ሀሳብ የችግኝ ተከላ መርኃግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በዛሬው እለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ክልል የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርኃግብርን በይፉ አስጀምሯል።

ከችግኝ ተከላ ፕሮግራም በኋላ የሚዛን አማን አየር ማረፊያ ግንባታን ለማስጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የመሠረት ድንጋይ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል::

(በሜሮን መስፍን)