ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ፈተና በድል ትሻገረዋለች – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሐምሌ 23/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ፈተና በድል ትሻገረዋለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በድል የምትሻገረውን ኢትዮጵያ ለማልበስ አረንጓዴ ዐሻራችንን እናሳርፍ ሲሉም ነው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያሰፈሩት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን ለማዳን እንዘምታለን፤ ኢትዮጵያን ለማልበስ እንተክላለን ብለዋል፡፡