ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን ሪፎርም ባህሬን እንደምትደግፍ ገለጸች

ጥቅምት 02/2014 (ዋልታ) ባህሬን ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን ሪፎርም እንደምትደግፍ የባህሬን የገንዘብና የብሔራዊ ኢኮኖሚ ሚኒስትር  ሼክ ሰሊማን ቢን ከልፋ አልካልፋ ገለጹ፡፡

ሚኒስትር ሼክ ሰሊማን ቢን ከልፋ አልካልፋ በኢትዮጵያ ህዝቦች ይሁንታ ያገኘው ዲሞክራሲያዊ መንግስት ምስረታ በጥሩ ሁኔታ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

ለአቻቸው አቶ አህመድ ሺዴ የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ በመሾማቸው የደስታ መልዕከት አስተላልፈዋል።

በባህሬን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት መሪ አምባሳደር ጀማል በከር ጋር የሁለትዮች የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ ትብብር በሚጠናከርበት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት ግንኙነትና ትብብር ይበልጥ በሚጠናከርበት ዙሪያ ተቀራርበው ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡