ተቋማቱ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

ጥቅምት 02/2014 (ዋልታ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

ተቋማቱ ስምምነቱን ያደረጉት አለምአቀፍ ገበያው በሚፈልገው መጠን ብቁ ባህረኞችን አሰልጥኖ ለአለምአቀፍ ገበያ ለማቅረብ መሆኑ ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሀና (ፕ/ር) ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ ተሳታፊ መሆኑ ለአለም አቀፍ ገበያ ተመራጭ የሆኑ ባህረኞችን ለማቅረብ ይረዳል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሮባ መገርሳ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያዊ ባህረኞችን ለውጪ ገበያ በማቅረብ በዓመት ስምንት ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማስገባት እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡

አክለውም ዘርፉ በተገቢው መንገድ ከተሰራበት በዓመት እስከ 250 ሚሊየን ዶላር ማስገባት ይቻላል ብለዋል።

በመስከረም ቸርነት