ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በማግኘቷ የእንኳን ደስ አለን መልዕክቶች እየተላለፉ ናቸው

ሐምሌ 23/2013 (ዋልታ) – በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ማስገኘቱን ተከትሎ የእንኳን ደስ አለን መልዕክቶች እየተላለፉ ይገኛሉ፡፡

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘዉዴ “እናት ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር ሰለሞን ባረጋ በቶክዮ ምድር  በ10,000 ሜትር የመጀመርያውን የወርቅ ሜዳልያ በማስገኘት ከፍ አደርጎሻል” ሲሉ የእንኳን ደስ አለን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቶክዮ በተገኘው ድል የእንኳን ደስ አለን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡