ኢትዮጵያ ያስተናገደችው የአኖካ ጉባኤ ዝግጅት ስኬታማ እንደነበር ተገለጸ

ኢትዮጵያ ያስተናገደችው የአኖካ ጉባኤ ዝግጅት ስኬታማ እንደነበር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ገለጹ።

የአኖካ ጉባኤ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሽልማትና የምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል።

በምሰጋና ፕሮግራሙ ላይ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ድንቁን ጨምሮ የሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት ጽ/ቤት ኃላፊዎች አና የስፖርት ሚዲያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለ2020 ቶኪዮ ከፍተኛ በጀት ዕቅድ እዲያዝ ማድረጋቸው እና በኃይል ወደቤተመንግሥት የመጣውን ወታደር ፑሽ አፕ አሠርቶ ማረጋጋት መቻላቸው በአኖካ ከፍተኛ ሽልማት እንዳበቃቸው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ፕረዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ተናግረዋል።

አቶ ኤሊያስ ሸኩርም ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለስፖርት ያላቸው ሀሳብ እና ተግባራት የአኖካ ሽልማት እንዲያገኙ ያስቻላቸው ሲሆን፣ ሽልማቱ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ክብር ነው ማለታቸውን ከፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡