ኢትዮጵያ 2ኛ ዙር የውኃ ሙሌትን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እያከናወነች ነው

ሰኔ 29/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ የታላቁን የሕዳሴ የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እያከናወነች እንደምትገኝ የህዳሴው ግድብ ቴክኒክ ኮሚቴ ተደራዳሪ ኃላፊ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው አስታወቁ፡፡

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር ሙሌት 2013 ዓ.ም ክረምት ላይ እንደምትጀምር ገልጻ እንደነበር ኢንጅነሩ ከዋልታ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ አብራርተዋል፡፡