ሰኔ 07/2013 (ዋልታ) – የገንዘብ ሚኒስቴር እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ኤጀንሲ እንዲሁም የኢትዮ-ቴሌኮም የቦርድ አማራር በተገኙበት ኢትዮ-ቴሌኮም በከፊል ወደ ግል ይዞታ የማዘዋወር ምዕራፍ የተጠናቀቀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም የ40% ድርሻ ለመሸጥ በሂደት ተሳተፊ መሆን የሚፈልጉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎች የፍላጎት መግለጫ ከነገ ሰኔ 08 ቀን 2013 ጀምሮ ማስገባት እንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡
የፍላጎት መግለጫው ለአንድ ወር የሚቆይና ዝርዝሩም በገንዘብ ሚኒስቴር እና በመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ እንደሚለቀቅ ተገልጻል፡፡
በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ተወዳዳሪ ባለሀብቶችን በአፍሪካ ትልቁ በሆነው የኢትዮ-በከፊል በማዛወር ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ ቀርቧል፡፡
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዕቅድ ጥያቄያቸውን የሚያስገቡ ሲሆን ይህም አጠቃላይ ሂደቱ ወቅቱን የጠበቀ፣ ቀልጣፋ እና የተስተካከለ አሰራርን በመያዝ የሚገለጽ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡