ሚያዝያ 11/2013 (ዋልታ) – የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ከዓለም ባንክ የምስራቅና የደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሩ ለዓለም ባንክ ኃላፊው በማዕድን ዘርፉ እየተከናወነ ካለው የፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያና ሪፎርም ጋር በተያያዘ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
የአለም ባንክ በማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ እንደሚያደርግ ኃላፊዎቹ መግለጻቸውን ከሚኒስትሩ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡