ኤጀንሲው በሰው ሀይል ፍሰት ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ እያደረገ ነው

ነሐሴ 11/2013 (ዋልታ) – የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በ2013 ዓ.ም በሰው ሀይል ፍሰት ላይ ያደረገውን ጥናት ለባለድርሻ አካላት ይፋ እያደረገ ይገኛል።

በጥናት መሰረት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተደረገው የሰው ሀይል ተሳትፎ ምጣኔ 65 በመቶ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በዚህም አንድ መቶ ለስራ ከደረሱ ሰዎች ውስጥ 65 የሚሆኑት በምርት ስራ ለመሰማራት ዝግጁ እንደሆኑ በጥናቱ ተመላክቷል።

የጥናቱ ዋና ዓላማ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት እንደሚረዳ የተገለፀ ሲሆን ለጥናቱ መሳካት አለም አቀፋ የፍልሰተኞች ድርጅት አይኦኤም “iom” እገዛ እንዳደረገ ተጠቁሟል።

ጥናቱ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች ከጥር እስከ የካቲት 2013 የተካሄደ ነው ተብሏል፡፡

(በሱራፌል መንግስቴ)