ነሐሴ 28/2013 (ዋልታ) ሰቆጣን የአማራ ልዩ ኃይል ከአሸባሪው ቡድን ነፃ ማውጣቱን የክልሉ የሰላም እና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) አስታወቁ።
በደቡብ ወሎ ዞን የወጣቶች የክተት መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ኃላፊው ቀጣይ አዲስ ዓመትን የምንቀበለው የሕዝብ እና የአገር ጠላትን በመቅበር ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ሃይቅ ከተማ ለመግባት ቋምጦ የመጣው የአሸባሪው ኃይልም ሙት እና ቁስለኛ ሆኖ ተመልሷል ብለዋል።
በሌሎች አካባቢዎችም የወገን ጦር ቁልፍ ወታደራዊና ስልታዊ ቦታዎችን ስለያዘ የሽብር ቡድኑን በገባበት ሁሉ መቀበሪያው እያደረገው እንደሆነ ገልፀዋል።
ኃላፊው ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ለመገንባት ወጣቱ መከላከያን እና ልዩ ኃይልን ሊቀላቀል ይገባል ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
የልዩ ኃይሉን አደረጃጀት ለማጠናከር ልዩ ትኩረት በመስጠትም የአማራ ክልል መንግሥት የማሰልጠኛ ካምፖችን በማዘጋጀት የወጣቶችን መግባት እየተጠባበቀ ነውም ነው የተባለው፡፡