” ከብዙ ፈተናዎች ጋር እየተጋፈጥን ሳለ ኢኮኖሚያችን ጽኑ በሆነ መልኩ እየተጠናከረ ነው ” – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጥር 22/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ጋር የስድስት ወር አፈፃፀም ግምገማ ማድረግ ጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቱሪዝም ዘርፉን ለማጎልበት የገበታ ለሀገር አካል በሆነው ሐላላ ኬላ ውብ ቦታ ላይ በመገምገም ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከብዙ ፈተናዎች ጋር እየተጋፈጥን ሳለ፣ ኢኮኖሚያችን ጽኑ በሆነ መልኩ እየተጠናከረ ነው ብለዋል::

በመሆኑም ይበልጥ አጠናክረን ለመቀጠል ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች በትብብር ምርታማነት ላይ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡