ከተማ አስተዳደሩ ለጎፋ የባህል ማዕከል የግንባታ ቦታ ሰጠ

ጥቅምት 7/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጎፋ የባህል ማዕከል የግንባታ ቦታ አስረከበ።

በርክክብ መርሃ ግብሩ የጎፋ እድገትና ብልጽግና ማኅበር የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ በይፋ ተመስርቷል።

በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ እየተከናወነ ባለው መርሃ ግብር የከተማ አስተዳደሩ ለጎፋ የባህል ማዕከል ግንባታ 5 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ አስረክቧል።

በርክክቡ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጎፋ ተወላጆች፣ የዞኑ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ወጣቶች መታደማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡