ሐምሌ 07/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 በጀት 70 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እንዲሆን ወስኖ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በበጀቱ ላይ ወይይት እያካሄደ ይገኛል::
የከተማ አስዳደሩ ካቢኔ በትናንትናው እለት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ በጀቱ 70 ነጥብ 6 እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል፡፡
የ2014 በጀት ድልድል በ2013 በጀት ከተያዘው ጋር ሲነፃፀር 9 ነጥብ 3 ቢሊየን ወይም የ15 በመቶ እድገት አለው ተብሏል።
ከተማ አስተዳደሩ የቀጣይ 10 እና 5 አመት ዓመታት መሪ እቅድን የተመለከቱ የትኩረት አቅጣጫዎችን እና ስትራቴጂ ግቦችን መሠረት ባደረገ መልኩ የ2014 በጀት አመት ለኮንስትራክሽን፣ ለውሃ እና ፍሳሽ፣ ለመንገድ ልማት፣ ለትምህርት እና ስልጠና፣ ለትራንስፖርት፣ ለአረንጓዴ ልማት፣ ለጤና እና ለቤቶች ልማት ዘርፍ እና ለሌሎችም ወጪዎች በጀቱ የሚውል መሆኑን አስታውቋል፡፡
(በሜሮን መስፍን)