ከተማ አስተዳደሩ ከ250 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የቁሳቁስ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ


ሐምሌ 20/2013 (ዋልታ) –
ሁላችንም ለኢትዮዽያ ወታደሮች አንድም በግንባር አንድም በደጀን ከጎናቸው ነን በሚል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ250 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊት አድርጓል::
ከዚህ ባለፈም ሀገርን ለማዳን የዘመተውን የሀገር ደጀን የሆነውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በፍቃደኝነት ለመቀላቀል የቆረጡ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ሽኝት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ሽኝት እየተደረገ ይገኛል::
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችም ለሀገር ህልውናን የዘመተው ለመከላከያ ሰራዊት ከቁሳቁስ አንስቶ እስከ ደም ልገሳ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል::
በድጋፍ መርሀ ግብሩም ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ቀንአ ያደታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል::
(በሔብሮን ዋልታው)