ተጨማሪ ስድስት የፓስፖርት የመቀበያ ቦታዎች ይፋ ሆኑ


ሐምሌ 19/2013 (ዋልታ) –
የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ተጨማሪ ስድስት የፓስፖርት የመቀበያ ቦታዎችን ይፋ አድርጓል።
ከዚህ ቀደም የፓስፖርት መቀበያ ቦታ ዋናው ፖስታ ቤት ብቻ የነበረ መሆኑን ያስታወሰው ኤጀንሲው፣ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ተጨማሪ ቦታዎችን ማዘጋጀቱን ገልጿል።
በዚህም መሠረት ተገልጋዮች የስም መነሻ ፊደላቸውን (የእንግሊዝኛውን) መሠረት በማድረግ ፓስፖርታቸውን መቀበል የሚችሉባቸውን ቦታዎች በዝርዝር አስቀምጧል።
አዲሶቹ የፓስፖርት መቀበያ ቦታዎቹ፦
ዋናው ፖስታ ቤት ፊደል፦ የስም መነሻ ፊደል፡ A, M, Q, R, S, X, Y, Z
አራት ኪሎ ፖስታ ቤት፦ የስም መነሻ ፊደል፡ E, F
አራዳ ፖስታ ቤት፦ የስም መነሻ ፊደል፡ B, C, D
ልደታ ፖስታ ቤት፦ የስም መነሻ ፊደል፡ G, H, I
ሰንጋ ተራ ፖስታ ቤት፦ የስም መነሻ ፊደል፡ J, K, L
አፍሪካ ጎዳና (ደንበል) ፖስታ ቤት፦ የስም መነሻ ፊደል፡ N, O, P
ካዛንችስ ፖስታ ቤት፦ የስም መነሻ ፊደል፡ T, U, V, W ናቸው።
በስም ፊደል የሆነው መቀበያ ቦታ ጊዜያዊ መፍትሔ መሆኑን ያስታወቀው ኤጀንሲው፣ ቀጣይነት ያለው መፍትሔ ኦንላይን በሚሞሉበት ጊዜ ሲስተሙ እነዚህን አዲስ መቀበያ ቦታዎች እንዲያስመርጣቸሁ ሆኖ በመገንባት ላይ ነው ብሏል።
የግንባታ ሂደቱ ጥቂት ጊዜያት ስለሚወስድም በትዕግሥት እንዲጠብቁ የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ጠይቋል።