ኅዳር 13/2014 (ዋልታ) የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር “እኔም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ነኝ” በሚል ድጋፍ ሲያሰባስብ ቆይቶ በዛሬው እለት ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ለመከላከያ ሰራዊት የርክክብ ስነ ሥርአት እያካሄደ ነው።
በርክክብ ስነ ሥርአቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሽታዬ መሀመድ እንዲሁም የአገር መከላከያ ሰራዊት አመራሮች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም ለኅልውና ዘመቻ ወደ ግንባር የሚዘምቱ ከአንድ ሺሕ በላይ የክፍለ ከተማው ወጣቶች እና የቀድሞ ሰራዊቶች አሸኛኘት እየተደረገላቸው ነው፡፡
በሜሮን መስፍን