ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

                         ንጉሤ መሸሻ (ዶ/ር)
በክብሯና በአንድነቷ እንድትኖር ቀደምት አባቶቻችንና እናቶቻችን በየዘመናቱ እየወደቁላት የኖረች ሀገር ናት ኢትዮጲያ። ዛሬም ስለሀገራቸው ሲሉ ጀግኖች ለክብሯና ስለአንድነቷ ይወድቃሉ፤ ለከፋፋዮች ሴራ ባለመሸነፍ።

የሀገራችንን ታሪክ እስከ 5000 ዘመን እንደሚደርስ ጸሀፍትና የታሪክ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ብዙዎች ግን የኢትዮጲያ ታሪክ ጠቅለል አድርገው ከ3000 ዘመናት በፊት እንደሆነ ያስቀምጣሉ ። የኢትዮጲያ ታሪክ በዳማት የሓ ከሚባለው ስልጣኔ የሚዘልቅ እንደሆነ በዚያም ሰፊ ግዛት የያዘ መንግስት (empire) በታሪክ የፑንት መሬት(Punt land)የሚባለውን ይዞ፣ ግብጽና የመንን ጨምሮ ወደ ደቡብ የተዘረጋ በጣም ሰፊ ቦታ እንዲሚያጠቃልል ቀደምት የግሪክ ጸሐፊዎችና ሌሎች የታሪክ ተመራማሪዎች ያስቀምጣሉ።

ለምሣሌ ፓወል ቢ ሔንዝ (2000) በ Layers of Time:

A History of Ethiopia መጽሐፍ ውስጥ የኢትዮጲያን ታሪክ በስዕሎችና በድንጋይ ላይ ጽሑፎች መሠረት 4000-5000 ዓመታት የሚዘልቅ እንደሆነ፤ ከዘር ሰው መገኛነት አኳያ ደግሞ ብዙ ሚሊዮን አመት ያላት ሀገር ናት ሲል ያትታል። እንዲሁም የአክሱም ስልጣኔ በዓለም ላይ ካሉ የግሪክ፣ የፔሪዥያ (የባቢሎን-የዛሬዎቹ ኢራቅና ኢራን አካባቢዎች)ና የቻይና ስልጣኔን ጨምሮ በዓለም ላይ ሦስተኛው ስልጣኔ ነው “pictorial records reveal aspects of its history extending back well beyond 4,000 years. Petroglyphs take it back at least another 5,000 years. Archaeology and paleontology bring the country’s history back millions of years” በማለት ይገልጻል።

በተጨማሪም Encycopedia Britanicca (2021) ስለቀደምት የኢትዮጲያ ታሪክ እንዲህ በማለት ይገልጻል። ኢትዮጲያ ቀዳሚ የስልጣኔ ሀገር ስለመሆኗ ሲያስቀምጥ ስለአክሱም ዘመነ መንግስት ይጠቅሳል። የአክሱም ስልጣኔ የሚባለው በጣም ሰፊ ቦታ የሚያጠቃልልና የሰሜንና የምስራቅ አፍሪካ የገበያ እንብርት እንደነበረ፣ ግዛቱም እሰከዘይላ እንዲሁም የአሁኗን ሶማሊያና ጅቡቲን ጨምሮ እሰከ ታች የሚወርድ ቦታን የሚይዝ እንደነበረ “The kingdom of D’mt [ዳማት] with its capital at Yeha was the first kingdom known to have existed , 10th century BC…the oldest standing structure in sub-Saharan Africa.. [stretching to] modern day Yemen” በማለት አስቀምጧል።

በተጨማሪ ከሰሜን በኩል የጥንታዊ ሮም ባይዛንታይን ስልጣኔና የፔርዢያ (የዛሬዎቹ ኢራቅና ኢራን አካባቢዎች) ስልጣኔ መሀል የሚገኝ እንደሆነ፤ ግብጾችም የመጡት የኢትዮጲያ አካል ከነበረው ከጥንታዊ የፑንት ምድር እንደነበረ Early and Later History of Ethiopia (2019) “The ancient Egyptians may have come from Ethiopia in about 3000 BC from a legendary land called Punt” በማለት ያስቀምጣል።

ይሄ ሁሉ የሚያስረዳን በስልጣንና ታሪክ ሽሚያ ኢትዮጲያ አንዳንዴ እየጠበበች አንዳንዴም ስትሰፋ የኖረች ሀገር ብትሆንም ከጥንት ጀምሮ እንደሀገር እንድትኖር ጀግኖች ልጆቿ መስዋዕት የከፈሉላት፣ ልጆቿ እየወደቁላት ብዙ ውጣ ውረዶችን እያለፈች በጽናት የቆመች ሀገር እንደሆነች ከታሪክ እንረዳለን ። ይህም የሚሆነው እንደ ሣሙኤል ፒ ሐንቲንግተን (1996) በስልጣኔ ሽሚያ Clashes of civilization ማንነትን መሠረት በሚያደረጉና በሚፈጠሩ ጦርነቶች ነው። ይሄ ደግሞ የሀገራችንን ታሪክ ስንመለከት እውነታነቱ የጎላ እንደሆነና ብዙ ውጣ ውረዶችን ከማንነት ጋር በተገናኘ ሀገራችን እንዳሳለፈች የምናውቀውና በቀጣይም ይሄው ትልቅ ፈተና እንደሚሆንብን ያሳያል።

በእርግጥም ኢትዮጰያ በውጭ ተጻራሪ ኃይሎች ጫና የተነሣ በየጊዜያቱ የካርታ ስፋትዋ በተለይ ከክርስቶስ መወለድ በኃላ ከንጉሥ ካሌብና ኢዛና ዘመናት ጀምሮ ሰፊ ቦታ ይዛ የነበረች ሀገር ይዞታዋ እያነሰ መጥቶ በቅኝ ግዛትና በነገስታቱ መለያየት ምክንያት በቀጣይ ግዜዎቿ (የህንድና ቻይና ሀገራት በተለየ የዘመናት ድንበራቸውን ሳይነጣጠሉ ማስቀጠል ሲችሉ )በግልጽ ባይታወቅም ግዛትዋ እያነሰ መጥቶ ይሄ ምናልባት የባዛንታይን ግዛት (Byzantine Empire) ሲያበቃ ከቱርኮች ግዛት (Ottman Turkish empire) መስፋፋትና ወረራ እንዲሁም ከቅኝ አገዛዝ ጋር በተገናኘ የእንግሊዝ የቅኝ ግዛት ውስጥ የወደቁት ሱዳን፣ ኬንያ፣ ሩወንዳ፣ ታንዛኒያን፣ ዩጋንዳና ሌሎች ሕዝቦችን ጨምሮ በያዘችበት ወቅት ድንበሯ እጅግ እንዲጠብ ተደርጓል። ለዚህም ማስረጃ ከሆነ World Atlas እንደሚነግረን አፍሪካ የሚለው ቃል ኢትዮጵ ከሚለው ጋር ያገናኙታል፤ ይሄም “the original ancient name of Africa was Alkebulan. This name translates to “mother of mankind,” or “the garden of Eden.” ይህ አህጉር እንዲሁ Ethiopians, Nubians, Moors, and Numidians በሚሉ ስያሜዎችም የሚጠራ ሲሆን የሰብልና የፍራፍሬ ምድር የሚል ትርጓሜ ያለው እንደሆነ World Atlas ይገልጻል። ይሄ ደግሞ አህጉሩን የውጭ ተስፋፊዎች ከመምጣታቸው በፊት Ethiopians ይባል እንደነበረና የስነምድር ካርታዎች ላይም ተቀምጦ የምናየው ነው።

የሰው ልጅ መገኛዋ -ምድረ ቀደምቷም እንደዚሁ ኢትዮጲያ ናትና አፍሪካ “mother of mankind” የሚለው ኢትዮጲያን የሚገልጽ ይሆናል። እንዲሁም ህዝቡ አንድ ስለመሆኑም ከጋራ Afro- Asiatic የቋንቋ ግንድ፣ አኗኗር፣ ባህል አንጻር ተመሳሳይ ህዝቦች እንደሆኑ የሚያመላክቱ ማንነቶች ያሉ መሆኑን ብዙ የህዝቦች የቅርጽ፣ የመልክ፣ የቀለም፣ ሌሎች ተመሳስሎዎች ያመለክታሉ።

ከአባይ ወንዝ ከመጠቀም ጋር በተገናኘ እንዲሁም እንግሊዞች በብዙ መልኩ የሶማሊያን፣ የኬንያንና የሱዳንን ቦታዎች በያዘቡት የቅኝ ዘመን ሁኔታ የዘመናዊ ኢትዮጲያን ካርታ ኤርትራንና ጁቡቲን ጨምሮ ይዘቱና ቅርጹ እንዲወሰን ማድረጉን የሰው ዘር አመጣጥ(paleoanthropology)፣ የሰነምድር ጥናት (geography)፣ የጥንት ጽሑፍ አጥኝዎች(Philologist እና folklorist)፣ የዘመናዊ ሰነጽሑፍ (litrature) አጥኝዎች፣ የታሪክና የፖለቲካ ሳይንስ ሙሁራን ይሞግታሉ ።

ከላይ የተገጹት የታሪክ ምንጮች በአንድም ሆነ በሌላ የኢትዮጵያን የታሪካ አመጣጥ የሚያሳዩና ከውጭ የሚደረጉ ጫናዎች ዛሬ ሀገራችን ለያዘችው ቅርጽ ወሳኝ እንደነበሩ ያሳያል።

ታዲያ ዛሬም ይህች ትልቅ ታሪክ ያላት ሀገር እንድትደክምና አልፎ ተርፎ እንድትፈርስ ዛሬ ላይም ብዙ ፈተናዎች ከፊታችን ተደቅነውብናል። ዛሬ በወገኖቻችን ላይ የሚደረግ ጥቃት፦ሞት፣ ንብረት መውደምና እንግልት፤ የውስጥ ኃይሎች ለስልጣን ሲሉ የሚያደርጉት የስልጣን ሽኩቻ አካልና ዛሬም ሊለያዩን ከሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች ሴራ የሚመነጭ መሆኑን ከላይ የቀረበው የታሪክ ዳራ ያሳየናል።

በመሆኑም ተጻራሪ የውጭ ኃይሎች ሁሌም ከራሳቸው ጥቅም አኳያ ተነጣጥለን ኢትዮጲያ የምትባል ሀገር እንድትዳከም ወይም እንድትጠፋ እኛኑን በማለያየት ሀዘናችንን የሚያብስና ልባችንን የሚያደማን ጉዳይ ይፈጽሙብናል። የወስጥ ተጻራሪ ኃይሎች ደግሞ ለስግብግብ የስልጣን ጥማቸው ሲሉ ሀገሪቷን በመቁረስ ትንንሽ መንግስታት መሆን ይፈልጋሉ። ይሄም ዛሬ ላይ በተበጀልን የብሔር ካባ ውስጥ ሆነን ከዚህ ወይም ከዚያ ብሔር እየጠቀሰን እንድንለያይ ተሰርቶብናል።

የዛሬው የህዝባችን ሞትና ስቃይ ከሀገሪቷ የታሪክ ሂደቶች ጋር በአንድም ይሁን በሌላ የተሳሰሩ ናቸው። የአሁኑ የህዝባችን ሞት የአንድ ብሔር ህዝብ ስለሆንን ተደርጎ መታሰብ የለበትም። በእርግጥ የአማራ ህዝብ የዛሬዋን ኢትዮጵያ ለማቆየት ከሌሎች ወንድምና እህት ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን በዘመናት ትግል ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይወሰዳል፤ ጆን ሶሬንሰን History and Identity in the Horn of Africa Vol. 17 (1992:227-252)።

የዛሬው የአማራ ህዝባችን ሞትና ግድያ የሁላችን የኢትዮጲያዊን ጉዳት ነው! የሌሎቹም ህዝቦቻችን ሞትና ስቃይ እንደዚሁ ያመናል። ይሄ ደግሞ የሀገራችንን ልዕልና በማይፈልጉ ብቻ ሳይሆን በውጭ ኃይሎች በሚደገፉ የውስጥ ኃይሎች እንዲሁም ሁለት ቦታ የሚረግጡ የወቅቶች የፖለቲካ ሰዎች ጭምር በሚደረግ የዕልቂት ደባ ሊሆን ይችላል።

ህዝቦች በማንነታቸው ሞትና ግድያ እንዲሁም ስቃይ ሊደርስባቸው አይገባም ነበር። ምክንያቱም ሁላችንም ከአንድ ግንድ የመጣን በዘመናት ቆይታ ግን የየራሳችን የምንላቸውን ቋንቋዎችና ባህሎች እያዳበርን የመጣን ህዝቦች ነን እንጂ።

በዘመናዊ የኢትዮጲያ ታሪክ የሕዝቦች የሻከረ ግንኙነት የመጣው የብሔር መብት አቀንቃኝ ኃይሎች ነን በማለት የብሔር አቀንቃኞች ከተፈጠሩበት ግዜ ጀምሮ ምናልባት በ1960ዎቹና 70ዎቹ ግዜያት ውስጥ ይሆናል ማለት ይቻላል። በወቅቱ የብሔር መብት አቀንቃኝ ኃይሎች የመንግስትን አገዛዝ ከመቃወም ባለፈ ፍትሐዊ ባልሆነ የፖለቲካ ትርክትና ቅኝት ሀገሬ ነው ብሎ በየአካባቢው ተሰራጭቶ የሚገኘውን ወይም በጭቆና ስርዓት ውስጥ ተሳትፎ የሌለውን በ”ብሔሩ” ማንነት ብቻ ከሌሎች ቋንቋዎች ህዝቦች ጋር አብሮ የሚኖረውን ህዝብ በማጥቃት በሚኖርበት ቦታ “አማራ” ተብሎ በጥላቻና በግፍ እንዲገደል፣ ሀብትና ንብረት በማውደም እንዲሁም በመዝረፍ እንዲሰቃዩ መደረጋቸው የ40 ወይም 50 ዓመታት ታሪክን ወደኃላ መለስ ብሎ በመጠየቅና በማንበብ መረዳቱ የሚበጅ ይሆናል። “አማራ” በግዜው ይባል የነበረው ከሌላ አካባቢ መጥቶ አማርኛ ይናገር የነበረውንም ጭምር ነበር።

ይሄን ጉዳይ እዚህ ላይ ለትንታኔ ሲቀርብ ቁርሾና ጥላቻን ለማኖር በማሰብ ሳይሆን ዛሬ ላይም ይሄ እየገጠመን በዕልቂት አዙሪት ውስጥ ሆነን ታሪክ እራሱን እንዲደግም እየተደረገ ሀገራችን እንድትፈርስ እያደረጉ እንደሆነ እየተገነዘብን ባለንበት ወቅት በመሆኑ ነው።

ይሔውም “ከዚህ ወይም ከዚያ ብሔር [ብሔር ግን ምንድነው? መመርመር ይፈልጋል] የመጣ ነው” በሚል በህዝባችን ላይ ሞት፣ ንብረት ማውደምና ስደት ሲደርስ እናያለን። ታዲያ ከአራት አስርት (ዓመታት) በፊትም በተመሳሳይ በሶማሌ፣ በሐረር፣ በባሌና በሲዳሞ ክፍለ ግዛቶች ወይም ክፍለ ሀገሮች በዚያን ዘመን የተደረጉ የማንነት ጥያቄዎች ጋር በተገናኘ የታጠቁ ኃይሎችና ተላላኪዎች ያንኑ ይፈጽሙ ነበር። በወቅቱ የህዝቦች መብትን በትጥቅ ትግል ማድረጉ ዋነኛ አማራጭ ተደረጎ ስለተወሰደ የብሔረ አቀንቃኝ ቡድኖች በዚያ መልኩ በመንግስት ላይ ያምጹ ነበር። ያ ትግል ስልት ግን ንጹሐን ዜጎችን ሞትና ስቃይ እንዲሁም የዜጎች ንብረት ውድመት በማስከተሉ ትልቅ ጠባሳ አሰቀመጠ እንጂ ስኬታማ መንገድ ግን አልነበረም።

እዚህ ላይ ልብ ያለው ልብ ይበል። በወቅቱ በታላቋዋ ሶማሌ የመመሥረት እሳቤ/ቅኝት ኢትዮጲያን ለማዳከምና ግዛት የማስፋት ስራ ከሶማሊያ በኩል ተደርጎ ነበር። ለዚህ የሲያድባሬ መንግስት መንሰራፋት በወቅቱ ሲያድባሬን ከአፍ እሰከ አፍንጫው ያስታጠቀው የአሜሪካ የግዜው መንግስት በጂሚ ካርተር 40 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተድርጎለታል ። ድጋፍ የተቸረውም የሶማሊያ መንግስትም በዚያ ግዜ የነበሩ የሀገራችን የብሔር ድርጅቶች ለብሔር እኩልነት ትግል በመነሳታቸው ምክንያት ቢሆንም እነሱን በሶማሊያ በኩል ለመጠቀሚያነት በማሰብ በግዜው እነዚያ የብሔር ድርጅቶች የተጠለሉት በዚያን ግዜ በነበረው ሱማሌ መንግስት እቅፍ ውስጥ ነበር። ይሄም ቀድሞ የእንግሊዞች ሶማሌን በቅኝ ይገዙ ስለነበረ የታላቋ ሶማሊያ አራማጅ የወጣቶች ሊግ ሴድሪክ ባረነስ (2007) እንደሚገልጸው እንዲመሰረት ሲረዱ የነበሩበት ፕሮጄክት አካል ነበር።

ታዲያ ከሶማሊያ የመጣው የወንበዴ ቡድን ደርግን የማዳክሚያ ስልት ያደረገው ሰርጎ በመግባት በአንድ ከተማ በአንድ ቀን ከ 50 አሰከ መቶ ዜጎች በመግደል፣ በብዙ መቶዎች ቤቶችን በማቃጠል፣ ቁጥር ስፍር የልላቸው የቁም ከብቶችና ንብረት በመዝረፍ ወደሶማሊያ-ሞቃዲሾ ይሸሽ ነበር። ይሄ ደግሞ በኦጋዴን፣ በሐርር፣ ቦረና፣ ባሌ፣ በመተከል፤ በሲዳማ፦አሮሬሣ፣ በንሣና አርቤጎና፣ በባሌ፦ ዶዶላ፣ አዳባ፣ ጊኒርና ከኮሳ አካባቢዎች ከውጭ በሚደገፉ ኃይሎች ሀገር ትታመስ ነበር። በወቅቱ ሲሞቱና ይገደሉ የነበሩት መጤ የተባሉ አማራና ሌሎች ወገኖችን ሲሆን ህዝቡን ለማስበርገግ ታስቦ ግድያዎች በማረድና በአሳቃቂ / ኢሰብዓዊ ሁኔታ ነበር። በሕይወት የዳኑትም ቢሆን አካባቢ ጥለው በብዙ ተሰደዋል፤ የብዙዎችም ንብረታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ወድሟል [ ይሄ ዛሬ ላይ በአጣዬ፣ መተከል- ቤንሻንጉል፣አፋርና ኢሳ፣ ምዕራብ ወለጋና ጉራ ፋርዳ ከሚፈጸሙ ግፎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው ይመስላል]።

በዚያ ወቅት በተለይ ነሐሴ 16, 1982 እኤአ የተደረገው የሲያድባሬ አሰከ አዋሽ ድረስ ዘልቆ ታላቋን ሶማሊያ የመመስረት ፍላጎት ጦርነት እንደ በጆርን ሙለር (2009) የእንግሊዞቹ በቅኝ ገዢ ዘመናት ህልም የነበረ፤ በኃላም የውክልና ጦርነት እንዲደረግበት ምክንያት እንደነበረ The Nework Times በገጹ Gureilla Drive in Somalia seems a proxy war በማለት የገለጸ ሲሆን እና ብዙ ዜጎች እንደሞቱና እንደተሰቃዩ በምክንያትነት ያስቀምጣል። ዛሬም የውክልና ጦርነት በኛ ላይ ለማድረግ እንደሚፈልግ ከሱዳን በኩል የሚመጣብንን በውጭ ኃይሎች የጭምር የሚደገፉ የውስጥ ተጻራሪ ኃይሎች መኖራቸውን መገንዘብ ይኖርብናል።ኢትዮጵያን ለመበታተን ቀደሞም ብዙ ችግሮቻችንን አስታከው መጠቀም የሚፈልጉ ሰርጎ ገቦች መኖራቸውን ለአፍታ መዘንጋት የለብንም። እኛኑ ከኛ የመነጣጠል ስራ በመስራት ነው። ጃኮብ ዞልማን የተባለው https://books.openedition.org/ እንደሚገልጸው ኢትዮጲያ በሠላም እንዳትኖር የተደረገው ከጎሮቤት ሀገራት ብቻ በሚመጣ ችግር ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን… ከ “Arab and then the Turkish expansions across the Red Sea and southwards beyond the Nubian Desert caused continual disputes over territories due to claims of competing empires”. የአውሮፓዋ ባለግዛት እንግሊዝም ሌላ ችግር ይዛ የመጣችው በ 1841, የመጀመሪያ ውል በ British Treaty of Friendship and Commerce ከግዜው ከነበሩት ንጉሥ ሣህለ ሥላሤ በማድረግ።

ኤርትራ የኢትዮጲያ አካል በነበረችበት ወቅትና እንግሊዝና ጣሊያን በዚያው በቆዩበትጊዜያት በብዙ የማራራቅ ስራ ተሰርቶብናል።ንጉሡ ኤርትራን ሙሉ ለሙሉ ከኢትዮጲያ ጋር ሲያዋህዱ University of Centeral Arkensas በ http://uca.edu/ እንዲሚገልጸው የሶሪያና ኢራቅ መንግስታት ሳይቀሩ የጦር መሣሪያ እገዛ ለኤርትራ ነጻ አውጪ ግንባር በ1963 እኤአ ይሰጧቸው ነበር። የሱዳንም መንግስት ከ 1964 እኤአ የጦር መሣሪያ እገዛ አድርገዋል። የቻይና መንግስትም እንደዚሁ ከመጋቢት 1967 እስከ 1970 እኤአ የጦር መሣሪያ እገዛ አድርጓል።

በወቅቱ ከሚደረጉብን ጫናዎች ጀርባ እየሆነ ያለው ምን ነበር? ለዚህ ምክንያቱ ምንስ ይሆን? መጠየቁ ተገቢ ነው። ይሄም ዛሬ በሀገራችን በቅርቡ የምናያቸው ሰው ሰራሽ ችግሮች ሁሉ ምንጫቸው ምን ይሆናል ብለን አስበን እንድንሰራ ያግዘናልና ነው።

የእኛ የኢትዮጲያዊነት መገለጫችን መተዛዘን ፣ መደጋገፍና አብሮ መኖር ሆኖ ሳለ እርስ በእርስ ለምን ተጨካከን!?።

ታዲያ ዛሬ ላይ የግፍና የበደል ገፈት ቀማሾችና የሞት ጽዋ እንድንጎነጭ የሆነብን በምን ይሆን? ምንስ ማድረግ ይኖርብናል!?

  1. ከላይ እንደተገለጸው ውስጣችንን፦ የጋራ ማንነታችንንና አብሮነታችንን በጎሣ (ethnic)፣ በቋንቋና በሐይማኖት ወዘተ መለያያ መንገዶች ህዝቦችን ከመሰል ህዝቦች ጋር እንዳይቀራረቡ፣ የማንነት አጥር በመፍጠር፣ አንዱ ከሌላው የተለየ እራሱን አድርጎ እንዲያስብ፣ አንድነት እንዳይፈጥርና በአንድ ወሰነ ምድር ብቻ ውስጥ ሆኖ እንዲያስብ በቅርብ ያለውን ወንድምና እህቱን በጥርጣሬ እንዲያይ የሚያደርጉ አሰራሮች፣ የትምህርት አሰጣጦች፣ ያም የኔ የም የኔ ብቻ በማለት የጋራ ማንነት መፍጠር እንዳንችል እየተደረገብን ነው። ይሄን አውቀን አንድነታችንን ማጠንከር ያስፈልጋል ።
  2. የትምህርት ስርዓታችን ከኛ የተቀዳ እንዳይሆንና ምዕራቡን የመሰለ ትምህርት በመሆኑ የከፋ ተፅዕኖ ውስጥ እንድንገባ ሆነናል። እንደ Jimmy Chulu(2015:15) “Today’s development in Africa is largely influenced by foreign culture, especially western culture” በዚህም የምዕራቡ ዓለም አፍቃሪ በመሆን የራሳችንን እንድንጠላ ተደርገናል ።
  3. የአባይ ወንዝ ባለቤት መሆን ከቅኝ አገዛዝ ግዜ እንዲሁም ከዚያም ቀደም ብሎ ባለ ግዜ ለመቆጣጠር ተብሎ ሀገርን የመከፋፈል ስራ በቅኝ ገዢዎቹ ተሰርቶብናል፤ ይሄም የሆነው “Control of the Nile has long been a matter of dispute”, John Waterbary (1979) እንደገለጸውና Marina Ottaway ( 2020) በEgypt and Ethiopia: The Curse of the Nile እንዳስቀመጠችው ዛሬ ላይም ይሄው ፈተና ቀላል አይደለም። ለዚህም አልሲሲ Alijazeera ሚያዚያ 07 /2021 የተናገሩትን ማየቱ ይጠቀማል ። “ማንንም ለማስፈራራት አይደለም። …አንድ ጠብታ ውሃ ከግብጽ ውሀ ከተወሰደ በቀጠናው ተገማች ያልሆነ አለመረጋጋት ይፈጠራል ብለዋል። “I’m not threatening anyone here….,” el-Sisi said. “I say once again no one can take a drop from Egypt’s water, and if it happens there will be “inconceivable instability” in the region። ሌሎች ሚዲያዎች ሮይተርስን ጨምሮ ይሄንኑ ዘግበውታል። በሌላ በኩል የውስጣዊ ችግሮቻችን በማየት ሱዳን ከግብጽ ጋር በመወዳጀት በኛ ላይ ተነስተዋል “Sudan, however, took advantage of Ethiopia being distracted by the conflict in Tigray last year and moved troops into al-Fashaga”እንደ ቢቢሲ ሚያዚያ 22/2021 ዘገባ።

ስለዚህ የኛ ምርጫ አንድና አንድ ነው እንደ H. Scaetta በ www.foreignaffairs.com እንደተገለጸው፦ The best defense of the Ethiopian people against invasion has always been the nature of the country they inhabit ተረድተን በአንድነት መቆም አለብን። በመሆኑም በተቀደደልን ወጥመድ ውስጥ ወድቀን ሀገራችንን ሳናውቅ ለጠላት ሰጥተን ከረፈደ በኃላ እንዳናዝን እያንዳንዱ እርምጃችን በጥንቃቄ የተሞላ ሊሆን ይገባል!

(በዶ/ር ንጉሤ መሸሻ)