በዘጠኝ ወር ከ212.4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

ሚያዝያ 19/2013 (ዋልታ) – በ2013 በጀት ዓመት ባለው በዘጠኝ ወር 213 ቢሊየን 85ዐ ሚሊዮን 048 ሺህ 262 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 212 ቢሊየን 473 ሚሊየን 364 ሺ 061 መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡

በዚህም በበጀት አመቱ አፈጻጸም የተመዘገበው ውጤት 99 ነጥብ 36 በመቶ ሆኗል ተብሏል፡፡

አፈጻጸሙ ከ2ዐ12 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ29 ቢሊዮን 225 ሚሊዮን 528 ሺ 145 ብር ወይም 15 ነጥብ 95 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡

ከሀገር ውስጥ ታክስ ብር 128 ቢሊየን 171 ሚሊየን 912 ሺህ 306፣ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ብር 84 ቢሊየን 135 ሚሊየን 403 ሺህ 672 እንዲሁም ከሎተሪ ሽያጭ ብር 166 ሚሊየን 048 ሺህ 082 በድምሩ 212 ቢሊየን 473 ሚሊዮን 364 ሺህ 061 ለመሰብሰብ መቻሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በወቅቱ ግብራቸውን የከፈሉ ግብር ከፋዮች፤ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የሌሎች አጋር አካላት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡