ከንቲባ አዳነች የመውሊድ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ጥቅምት 7/2014 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመውሊድ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው “በአሉን ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩትን በመርዳት፣ ያለንን ለሌሎች በማካፈል፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የወደቁትን በማንሳት፣ የታመሙትን በመዘየር፣ ለምድራችን ሰላም ዱአ በማድረግ እንዲሆን እመኛለሁ” ብለዋል።