መንግስት የሀገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል ከታህሳስ 02/2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/2013 ዓ.ም ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የአውሮፕላን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት ከነበረው በሊትር 25.37 በዓለም ወቅታዊ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ በተገኘው ልዩነት 10 ሳንቲም ጨምሮ በሊትር ብር 25.47 እንዲሸጥ የተወስኗል።
በአለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግም እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚችል ተገልጿል፡፡