መጋቢት 3/2013 (ዋልታ) – ከፀሃይ ሃይል 500 ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡
ስምምነቱ በአቡ ዳቢው ማስዳር እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል መፈረሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡
ስምምነቱ ኢትዮጵያ ካላት ሃይል የማምረትና የማመንጨት አቅም አኳያ የሃገሪቱን የግል እና የመንግስት ትብብር የማጠናከር ጥረት በትግባር የሚያሳይ ነውም ብለዋል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ ከፀሀይ ሀይል 500 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ ፕሮጀክት ወደ ስራ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ከታዳሽ ሀይል ኤሌክትሪክ የማመንጨት እና የማሰራጨት ከፍ ያለ ልምድ እንዳላትም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያስታወቁት።