የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የለውጥ ስራዎች መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

መጋቢት 03/2013 (ዋልታ) – የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን እንደቁልፍ አጋር እንደሚቆጥራት እና በአገሪቱ የሚካሄዱ የለውጥ ስራዎች መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

በቤልጄም ብራስልስ በአውሮፓ ህብረት ፅህፈት ቤት ፊት ለፊት በትላንትናው እለት የኢትዮጵያን ትክክለኛ እና ወቅታዊ ገፅታ ለመላው ዓለም ለማስተጋባት የተደረገውን ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፍ ህብረቱ እንደተመለከተውም አስታውቋል።

ህብረቱ የኢትዮጵያውያንን ፍላጎት ጠንቅቆ እንደሚረዳ እና ለአገሪቱ የሚያደርገውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ክልል ያለው የሰብአዊ ቀውስ እንደሚያሳስበው ያስታወቀ ሲሆን ዓለም ዓቀፉን የስደተኞች እና የሰብአዊ መብት ሕግጋት በክልሉ እንዲከበርም ጥሪ አቅርቧል።