ከ33.4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ33.4 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በገቢ እና ወጪ ኮንትሮባንድ 33 ሚሊየን 430 ሺህ 62 ብር የሚገመት ዕቃ ከህዳር 18 እስከ 24፣ 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከዚህ ውስጥ 31 ሚሊየን 253 ሺህ 301 ብር የሚገመተው ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር የተያዘ ሲሆን፣ ወደ ውጭ ሲጓጓዙ የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ግምታዊ ዋጋቸው 2 ሚሊየን 176 ሺህ 760 ብር መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት በፍተሻ፣ በብርበራ እና በተሽከርካሪ በመከታተል ነው ተብሏል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የጉምሩክ ሰራተኞች እና አመራሮች ከፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር በቅንጅት በመስራት በተለያዩ የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች  በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡