ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን ተመረጠች

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን ተመረጠች፡፡

ይህንንም ተከትሎ አትሌት ደራርቱ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ትመራለች፡፡

ከዚህ ቀደም ላለፉት ሁለት ዓመታት  የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን በማገልገል ላይ ነበረች፡፡

ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ድምፅ ባላቸው የጉባኤ አባላት በሙሉ ድምፅ ያለምንም ተቃውሞ ለፕሬዝዳንትነት ተመርጠው ያሸነፋ መሆኑን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡