ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ጥር 15 ተማሪዎቹን እንደሚያስመርቅ አስታወቀ

              ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

 

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የፊታችን ጥር 15 ተማሪዎቹን እንደሚያስመርቅ አስታውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ4 ኮሌጆች እና በ14 ትምህርት ክፍሎች በ2010 ዓ.ም ስራ የጀመረ ሲሆን፣ በወቅቱ ከተቀበላቸው ተማሪዎች መካከል 1 ሺህ የሚሆኑትን እንደሚያስመርቅ ነው ያስታወቀው፡፡

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዘዳንት  ረ/ፕሮፌሰር አንዋር አህመድ ለምረቃ መረሀግብሩ በቂ ዝግጅቶች የተደረጉ መሆናቸውን ለዋልታ ገልፀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ በ6 ኮሌጆች፣ በአንድ ኢንስቲትዩት እና በሁለት ትምህርት ቤቶች በአጠቃላይ 49 ፕሮግራሞች እያስተማረ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ማዳረስ መቻሉም ተጠቁሟል፡፡

በ2010 ቅበላ ካከናወኑ 11 ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የወራቤ ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑ ይታወሳል፡፡

(በደረሰ አማረ)