ነሃሴ15/2013(ዋልታ) – ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ለማሻሻል የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ በከተማዋ ካሉ የንግዱ ማህበረሰቦች ጋር ወይይት እያካሄዱ ነው፡፡
በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ተገኘተዋል፡፡
የኑሮ ውድነቱን ለማሻሻል ከንግዱ ማህበረሰብ ምን ይጠበቃል ፣ መንግስትስ መውሰድ ያለበት እርምጃ ምን መሆን አለበት በሚለው ላይ ነው ሰፊ ውይይት እየተካሄደ ነው የሚገኘው ።
ሀገርን ለማዳን የህልውና ዘመቻ ላይ እንደመሆናችን የንግዱ ማኅበረሰብ በዚህ ከባድ ወቅት ከትርፍ ይልቅ ለሀገር እና ለህዝብ ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባል ተብሏል ፡፡
(በሜሮን መስፍን)