በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቢዝነስ ዲፕሎማሲና የዲያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ከሩስያ-ሴንትፒተርስበርግ ከተማ ከመጡ የኢንቨስትመንት ልዑካን ጋር ተወያዩ፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ ባለሀብቶቹ ኢትዮጵያን ለኢንቨስትመንት ተማራጭ በማድረጋቸው አመስግነው፣ ለኢንቨስትመንት ያለውን ምቹ ሁኔታዎች አብራርተዋል፡፡
መዋዕለ ነዋያቸውንም በማፍሰስ ወደ ተግባር እንዲገቡ መንግሰት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ገልጸዋል፡፡
የልዑኩ መሪ የሆኑት ማርክ ሩስላን በበኩላቸው፣ በነበራቸው የስራ ጉብኝት ከማዕድን ሚኒስቴር፣ ከንግድ ሚኒስቴር፣ ከኮንስተራክሽን ሚኒስቴር፣ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዲሁም ከንግድና ዘርፍ ማህበራት በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበልና ውይይት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በሶስት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ኢንቨስት ለማድረግ ከኢነርጂ፣ ከኢኖቬሽንና ንግድና ዘርፍ ማህበራት ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም አብራርተዋል፡፡
ቡድኑ በተለያዩ አገራት በተግባር የተደገፈ እንቅስቃሴ እንዳለቸውና በጅቡቲ በቱሪዝም ዘርፍ ሰፊ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን በመግለጽ፣ በኢትዮጵያም በቀጣይ 3 ወራት ውስጥ ወደ ስራ እንቅስቃሴ እንደሚገቡማሳወቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡