ዓለም ዐቀፍ አደጋ ቅነሳ ቀን እየተከበረ ነው

ጥቅምት 5/2014 (ዋልታ) “አብሮነት ለምድራችን ደህንነት” በሚል መሪ ሀሳብ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቀን በኢትዮጵያ ለ12ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በኢትዮጵያ የተፈጥሮ አደጋ፣ ድርቅ፣ ጎርፍ፣ የአምበጣ መንጋ፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እንዲሁም በሰላም እጦት ሳቢያ የዜጎች መፈናቀል ተጠቃሽ ተግዳሮቶች መሆናቸውን ገልፀዋል።

በኮቪድ-19 የተጎዳውን የአፍሪካ ኢኮኖሚ በማነቃቃት የአደጋ ቅነሳ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቃልም ተብላል።

በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች በሚከሰቱ አደጋዎች ህፃናት ቀጥተኛ ተጠቂ መሆናቸውም ተገልጿል።

በ2030 የታቀደውን የአደጋ ቅነሳ ከግብ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የአፍሪካ ህብረትና  የኢጋድ ተወካዮች የታደሙበት መድረክ በአህጉሪቱ ያለውን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ቅነሳ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡

ቀኑ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ለ44ኛ ጊዜ የሚከበር ነው፡፡

በሀኒ አበበ