ኤጀንሲው በትግራይ ክልል ተማሪዎችን ለመፈተን ችግር እንደገጠመው ገለጸ

ጥቅምት 5/2014 (ዋልታ) በትግራይ ክልል ተማሪዎችን ለመፈተን ችግር እንደገጠመው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የፈተና አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ሳይጨምር 617 ሺሕ ተማሪዎችን የሚያስፈትነው የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና በማስመልከት የተለያዩ ሀሳቦች እየተሰጠበት ይገኛል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲሁም ሌሎች በሀገሪቱ ላይ የተፈጠሩ እክሎች ምክንያት በ2013 ዓ.ም ይሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና አለመሰጠቱ የተገለፀ ሲሆን፣ ፈተና አሰጣጡን የተሳካና ምንም አይነት ጥያቄ እንዳይነሳ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዙፋን አምባቸው