ዛሬ ምሽት በአውሮፓ ሻምፒዮንሽ ሊግ ሁለት ተጠበባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ

መጋቢት 3/2016 (አዲስ ዋልታ) ዛሬ ምሽት በአውሮፓ ሸምፒዮንስ ሊግ ሁለት ተጠባቂ የሁለተኛ ዙር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ካሄዳሉ።

ምሽት 5 ሰዓት አርሰናል በሜዳው ከፖርቹጋሉ ፖርቶ ጋር የምጋጠም ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ፖርቶ 1 ለ 0 ማሸነፉን ተከትሎ አርሰናል ውጤቱን የመቀልበስ ትልቅ ፈተና ይገትመዋል ተብሏል።

በሊጉ ጠንካራ አቋም እያሳዬ ያለው አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ ስታዲየም ስታደየም የሚያደርገውን ጨዋታ በድል እንደሚያጠናቅቅ የእግር ኳስ ባለሙያዎች አስተያዬታውን እሰጡ ነው።

እ. ኤ. አ ከ2010 ወዲህ ፖርቶ አርሰናልን በሜዳው አሸንፎት እንደማያውቅና ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር ካደረጋቸው 23 ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ነው ማሸነፍ የቻለው። በዚህም የዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ሊከብደው እንደሚችል ዘገባዎች ያሳያሉ።

በምሽቱ የሚደረገው ሌላው ጨዋታ በተመሳሳይ 5 ሰዓት ላይ የስፔኑ ባርሴሎና በሜዳው የጣሊያኑን ናፖሊን ያስተናግዳል። ሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ 1 ለ 1 መለያዬታቸው ይታወሳል።

በቴዎድሮስ ሳህለ