ዛሬ በሚካሄደው የምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባ የሚኒስትሮች ሹመት ይጠድቃል ተብሎ ይጠበቃል

መስከረም 26/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያካሂደው 6ኛ ዙር 1ኛ አመት 1ኛ ልዩ ስብሰባ የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ እንደሚያጸድቅ ተገልጿል።

ም/ቤቱ በልዩ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያቀረቡትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን ያደምጣል።

በተጨማሪም የፌዴራል መንግስት የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባርን  መወሰኛ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ተመላክቷል።

በመጨረሻም የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ በማጽደቅ የእለቱን ልዩ ስብሰባ ያጠናቅቃል ተብሏል።

ልዩ ስብሰባው ከጧቱ 3:30 በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በዋናው የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።