ታኅሣሥ 12/2014 (ዋልታ) በሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የተመራ ልዑካን ቡድን አፋር ክልል ሰመራ ገባ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች አፋር ክልል የገቡት በአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመጎብኘትና መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ አለኝታነቱን ለመግለጽ ነው ተብሏል።
በርዕሰ መስተዳድሩ ለተመራው የልኡካን ቡድን የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች በሰመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፍሬ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል ማድረጋቸውን ከብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በልዑካን ቡድኑ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ጨምሮ የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አብዱጀባር መሀመድ፣ የፌዴራል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተወካይ ካሊድ አልዋን እንዲሁም ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡