የሀረሪ ክልል ካቢኔ አባላት ለሁለተኛ ጊዜ ደሞዛቸውን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ለገሱ

ሐምሌ 17/2013 (ዋልታ) – የሀረሪ ክልል የካቢኔ አባላት ለሁለተኛ ጊዜ የአንድ ወር ሙሉ ደሞዛቸውን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ለገሱ።

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) አባላት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ነው አባላቱ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመስጠት የወሰኑት።

የካቢኔ አባላቱ ከወራት በፊትም የወር ደሞዛቸውን መለገሳቸው የሚታወስ ሲሆን የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ተወስቷል።

የመስተዳድር ምክር ቤት አባላቱ በቀጣይም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።