የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኮሮናን በመከላከል የምርት ሂደቱ እንዳይስተጓጎል እያደረገ ያለው ጥረት ለሌሎችም ተቋማት ምሳሌ እንደሚሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።
የኮሚቴው አባላት ፓርኩን በጎበኙበት ወቅት ቡድን መሪ አቶ ዘውዱ ከበደ እንዳሉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ፈሶባቸው የተቋቋሙት የሥራ ዕድል ፈጠራን ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እንዲሁም የውጭ ምንዛሪን ለማሳደግ ነው።
የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ከተማ በበኩላቸው ፓርኩ ተቆጥሮ የተሰጠውን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በፓርኩ ውስጥ ከ28 ሺህ ባለይ ሠራተኞች እንዳሉ ጠቁመው፤ኩባንያዎች ውስጥ በሚሰሩበት ወቅት የተሟላ የቴክኖሎጂ እውቀት እንዲቀስሙ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነም ተናግረዋል።