የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነት መርህን መሰረት በማድረግ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

ሐምሌ 2/2014 (ዋልታ) የሁለቱ እህትማማች ሀገራት ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነት መርህን መሰረት በማድረግ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለድቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት እንዲሁም በራሳቸው ስም ለደቡብ ሱዳን ሕዝብ እና መንግሥት እንኳን ለ11ኛ ዓመት የነፃነት ቀን በዓላችሁ አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የሁለቱ እህትማማች ሀገራት ግንኙነትም የጋራ ተጠቃሚነት መርህን መሰረት በማድረግ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን በደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW